=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
ምስጋናና ልቅና ለአሏህ ይገባው። አሏህ የመራውን ማንም አያጠምም፤ አሏህ ያጠመመውን ማንም አይመራም።
የአሏህ ሰላም እና እዝነት በነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በሶኻቦቻቸቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ የውመልቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።
አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል ኢምራን አንቀፅ 104 ላይ እንዲህ ይላል:-
=<({አል-ቁርአን 3:104})>=
{104} ከእናንተም ወደ በጐ ነገር የሚጣራ ፣ በመልካም ስራ የሚያዝ ፣ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ህዝቦች ይኑሩ። እነዚያ እነሱ የሚድኑ ናቸው።
እንዲሁም አሏህ በሱረቱል ፋሲለት አንቀፅ 33 ላይ እንዲህ ይላል:-
=<({አል-ቁርአን 41:33})>=
{33} ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?
በሰኺኽ ሙስሊም እንደተዘገበው የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ከእናንተ መካከል መጥፎን የተመለከተ በእጁ ያስቁም። ይህን ማድረግ ያልቻለ በምላሱ ያድርግ። ይህንን ማድረግ ያልቻለ ከልቡ ይጥላ። እናም ያ ትንሹ የኢማን ደረጃ ነው ብለዋል።
በመልካም ነገር ማዘዝና ከመጥፎ ነገር መከልከል በኢስላም ትልቅ ሃላፊነት ሲሆን ኡለማዎች ይህን የተቀደሰ ተግባር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው ብለዋል። ምክርን እንለዋወጥ ዘንድ ሌሎችን መልካም ወደሆነ ነገር እናመላክት ዘንድ እና እርስበርሳችነም እውነት በሆነ ነገርና በትዕግስት አደራ አደራ እንባባል ዘንድ ታዘናል። ደህንነታችን የሚረጋገጠው በዚህ ላይ ሲሆን እሱን ችላ ማለት ደግሞ ውጤቱ የከፋ ነው።
:☀:አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል አል-ዐስር ከአንቀፅ 1 እስከ 3 ባለው እንዲህ ይለናል:☀:
=<({አል-ቁርአን 113:1-3})>=
1 በጊዜያት እምላለሁ።
2 በእርግጥ ሰው ሁሉ በኪሳራ ውስጥ ነው።
3 እነዚያ ያመኑት ፣ መልካም ስራን የሰሩት ፣ በእውነት እና በትዕግስት አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።
እንደሚታወቀው ክረምት ሲጠባ ትምህርት ቤቶች ሁሉ ይከፈታሉ፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቇማትም በራፋቸውን ከፍተው ተማሪዎችን ያስተናግዳሉ። ሁሉም ዲፓርትመንቶችም ተማሪዎቻቸቸውን በwellcome fresh ይቀበላሉ። በዚህ ወቅት የሚሰራው ፋህሻ እጅግ የከፋ ሲሆን ወደ ሸይጧን መንገድ የሚጣራው በጣም ብዙ ነው። ታዲያ አንዳንድ ሙስሊም ሴቶችም ሆኑ ወንዶች በካንፓስ ውስጥ ሲኖሩ የብቸኝነት ወይም የነፃነት ስሜት ስለሚሳማቸው ሊሆን ይችላል አሉ የታባሉ ወንጀሎችን ሲሰሩ ይስተዋላል። ሆኖም ይህ አጋጣሚ የኢስላምን መልዕክት ለማስተላለፍ እራሳቸውን ላዘጋጁ ወንድሞች ትልቅ አጋጣሚ ነው። ቢሆንምግን ይህን ተግባር የካንፓሱ አሚሮች እንኴ ሳይቀሩ ችላ ሲሉት ይስተዋላል።
እውቀት ኖሮት እውቀቱን የደበቀ ሰው ጤቱ የከፋ ነው። በሐዲስ እንደተዘገበው አሏህ የውመልቂያማ ከጀሃነም እሳት በሆነ ልጏም እንደሚለጉምህ ወይም እንደሚለጉምሽ አትጠራጠሪ!!!
<> ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?
۩ በግቢያችን ውስጥ ወጣ ያለ ባህሪ ያላቸው እህት ወንድሞቻችን እነማናቸው?
۩ ዚያራ ሴክተር ላይ ምንያህል እየተሰራ ነው?
۩ በእያንዳንዱ ስራችን ላይ ምን ያህል ትብብር አለን?
۩ የዳዕዋ ሴክተር ድርሻ እስከምን ድረስ ነው?
۩ በዳዕዋ ሴክተርና በዚያራ ሴክተር ያለው ቁርኝት ምን ይመስላል? ሁለቱን ሴክተሮች አንድ ላይ እንዴት ማስኬድ እንችላለን?
۩ ጀመአችን ላይ አህላቃቸው የተበላሸ ሰብሴክተር ላይ ያሉ ሰዎችም ሆኑ አሚሮች እነማናቸው? ሙስሊም ተማሪዎች ከነዚህ ሰዎች ምን ይማራል?
۩ ፍሬሽ እህት ወንድሞቻችነን እንዴት ነው የምንቀበለው?
۩ ወደ ጀመዐችን ለማምጣትስ ምን ያህል ጥረት እናደርጋለን?
<> እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን በማንሳት መልስ ማፈላለግ እና ጠንካራ መሠረት ያለው ጀመአ ለመፍጠር መጣር ይኖርብናል!!!
ኢንሻ አሏህ! በክፍል ሁለት የሙስሊም ወጣቶች የዳዕዋ ጉዞ በሚል ርዕስ ስር እውን ወጣቶች ዳዕዋ ማድረግ ይችላሉን? ዳዕዋ ከማድረጋችን በፊት ልንላበሳቸው የሚገቡ ባህሪያት ምንምን ናቸው? እንዴትስ ዳዕዓውዋ ማድረግ እንችላለን? የሚሉ ንዑስ አርዕስቶችን እንዳስሳለን።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|